ምዕራፍ 128

የመዓርግ መዝሙር።

እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
2 የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።
3 ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።
4 እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
5 እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።
6 የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።