ምዕራፍ 34

ኤሊሁም ደግሞ መለሰ፥ እንዲህም አለ።
2 ፤ እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እናንተም አዋቂዎች፥ ወደ እኔ አድምጡ።
3 ፤ ትናጋ መብልን እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃልን ትለያለችና።
4 ፤ ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፤ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ።
5 ፤ ኢዮብ። እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርዴን አስወገደ፤
6 ፤ ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፤ ምንም ባልበድል ቍስሌ የማይፈወስ ነው ብሎአል።
7
8
9 ፤ ኢዮብም። በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሎአልና ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ መሳለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?
10 ፤ ስለዚህ እናንተ አእምሮ ያላችሁ ሰዎች፥ ስሙኝ፤ ክፋትን ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም ይሠራ ዘንድ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።
11 ፤ ለሰው ሥራውን ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።
12 ፤ በእውነት እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ፍርድን ጠማማ አያደርግም።
13 ፤ ምድርን አደራ የሰጠው ማን ነው? ዓለምንስ ሁሉ በእርሱ ላይ ያኖረ ማን ነው?
14 ፤ እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥
15 ፤ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል።
16 ፤ አስተዋይ ብትሆን ይህን ስማ፤ የንግግሬንም ቃል አድመጥ።
17 ፤ በውኑ ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን? ጻድቅና ኃያል የሆነውስ በደለኛ ታደርገዋለህን?
18 ፤ ማንም ሰው ንጉሡን። በደለኛ ነህ፥ መኳንንቱንም። ክፉዎች ናችሁ ይላልን?
19 ፤ እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና በአለቆች ፊት አያደላም፥ ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።
20 ፤ እነርሱ በመንፈቀ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ እጅ ይነጠቃሉ።
21 ፤ ዓይኖቹ በሰው መንገድ ላይ ናቸው፥ እርምጃውንም ሁሉ ያያል።
22 ፤ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሰወሩበት ዘንድ ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።
23 ፤ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመፈራረድ እንዲመጣ ጊዜ አይወሰንለትም።
24 ፤ ታላላቆችን ያለ ምርመራ ይሰባብራል፥ በእነርሱም ፋንታ ሌሎችን ያቆማል።
25 ፤ ሥራቸውን ያውቃል፤ እንዲደቅቁም በሌሊት ይገለባብጣቸዋል።
26 ፤ ሰዎች እያዩ እንደ ክፉዎች ይመታቸዋል፤
27
28 ፤ የድሀውን ልቅሶ ወደ እርሱ ያደርሱ ዘንድ፥ እርሱም የችግረኛውን ድምፅ ይሰማ ዘንድ፥ እርሱን ከመከተል ፈቀቅ ብለዋልና፥ ከመንገዱም ሁሉ አንዱን አልተመለከቱምና።
29 ፤ በሕዝብ ወይም በሰው ዘንድ ቢሆን፥ እርሱ ቢያሳርፍ የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?
30 ፤ ይህም ዝንጉ ሰው እንዳይነግሥ፥ ሕዝቡም የሚያጠምድ እንዳይኖር ነው።
31 ፤ እግዚአብሔርን። እኔ ሳልበድል ቅጣት ተቀበልሁ፤
32 ፤ የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፤ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው?
33 ፤ በውኑ አንተ ጥለኸዋልና ፍዳው አንተ እንደምትወድደው ይሆናልን? አንተ ትመርጣለህ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ ስለዚህ የምታውቀውን ተናገር።
34 ፤ የሚሰሙኝ ጥበበኞች ሁሉ፥ አስተዋዮችም እንዲህ ይሉኛል።
35 ፤ ኢዮብ ያለ እውቀት ተናግሮአል፥ ቃሉም በአእምሮ አይደለችም።
36 ፤ ኢዮብ እስከ ፍጻሜ ድረስ ምነው በተፈተነ ኖሮ! እርሱ እንደ ክፉዎች መልሶአልና፤
37 ፤ በኃጢአቱም ላይ ዓመፅን ጨምሮአልና፥ በእኛም መካከል በእጁ ያጨበጭባልና፥ ቃልንም በእግዚአብሔር ላይ ያበዛልና።