መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 9

እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ይሁዳም ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።
2 ፤ በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም ናታኒምም ነበሩ።
3 ፤ ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች ከኤፍሬምና ከምናሴ ልጆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
4 ፤ ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኒ ልጅ የአምሪ ልጅ የፆምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀመጠ።
5 ፤ ከሴሎናዊያንም በኵሩ ዓሣያና ልጆቹ።
6 ፤ ከዛራም ልጆች ይዑኤልና ወንድሞቻቸው፥ ስድስት መቶ ዘጠና።
7 ፤ ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤
8 ፤ የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የዪብኒያ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም፤
9 ፤ በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ።
10 ፤ ከካህናቱም ዮዳሄ፥ ዮአሪብ፥ ያኪን፤
11 ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ ሜሱላም ልጅ የኬልቂያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
12 ፤ የመልኪያ ልጅ የጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ፤
13 ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ወንድሞቻቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር ቤት ማገልገል ሥራ እጅግ ብልሃተኞች ሰዎች ነበሩ።
14 ፤ ከሌዋውያንም የሜራሪ ልጆች የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤
15 ፤ በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፤
16 ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰሙስ ልጅ አብድያ፤ በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ።
17 ፤ በረኞችም ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤልሞን፥ አሒማን፥ ወንድሞቻቸውም ነበሩ፤ ሰሎምም አለቃ ነበረ።
18 ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረኞች ነበሩ።
19 ፤ የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር።
20 ፤ አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።
21 ፤ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ የመገናኛው ድንኳን ደጅ በረኛ ነበረ።
22 ፤ የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ አሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።
23 ፤ እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።
24 ፤ በአራቱ ማዕዘኖች፥ በምሥራቅ፥ በምዕራብ፥ በሰሜን፥ በደቡብ፥ በረኞች ነበሩ።
25 ፤ ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባትም ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር።
26 ፤ ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የበረኞች አለቆች ዘወትር በሥራቸው ይቀመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ነበሩ።
27 ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።
28 ፤ ዕቃውም በቍጥር ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዱ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።
29 ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹ በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁ፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ።
30 ፤ ከካህናቱም ልጆች አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅባት ያጣፍጡ ነበር።
31 ፤ የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።
32 ፤ በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።
33 ፤ ከሌዋውያኑም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለሌላ ሥራ በየጓዳቸው ይቀመጡ ነበር።
34 ፤ እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።
35 ፤ የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥
36 ፤ የበኵር ልጁም ዓብዶን፥
37 ፤ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር፥ ሚቅሎት፥ በገባኦን ይቀመጡ ነበር።
38 ፤ ሚቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ይቀመጡ ነበር።
39 ፤ ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ።
40 ፤ የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
41 ፤ የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።
42 ፤ አካዝም የዕራን ወለደ፤ የዕራም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
43 ፤ ሞጻም ቢንዓን ወለደ፥ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤
44 ፤ ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓሪያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ልጆች ነበሩ።