መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 24

የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።
2 ፤ ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ።
3 ፤ ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓት ከፍሎ መደባቸው።
4 ፤ የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምርም ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
5 ፤ ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
6 ፤ ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቢሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
7 ፤ መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥
8 ፤ ሦስተኛው ለካሪም፥
9 ፤ አራተኛው ለሥዖሪም፥ አምስተኛው ለመልክያ፥
10 ፤ ስድስተኛው ለሚያሚን፥ ሰባተኛው ለአቆስ፥
11 ፤ ስምንተኛው ለአብያ፥ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥
12 ፤ አሥረኛው ለሴኬንያ፥ አሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፥
13 ፤ አሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥
14 ፤ አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፥
15 ፤ አሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፥ አሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፥
16 ፤ አሥራ ዘጠኝኛው ለፈታያ፥
17 ፤ ሀያኛው ለኤዜቄል፥ ሀያ አንደኛው ለያኪን፥ ሀያ ሁለተኛው ለጋሙል፥
18 ፤ ሀያ ሦስተኛው ለድላያ፥ ሀያ አራተኛው ለመዓዝያ።
19 ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደ ሰጣቸው ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ።
20 ፤ ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ሱባኤል፤ ከሱባኤል ልጆች ዬሕድያ፤
21
22 ፤ ከረዓብያ ልጆች አለቃው ይሺያ፤ ከይስዓራውያን ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ልጆች ያሐት፤
23 ፤ ከኬብሮንም ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛው ይቀምዓም፤
24 ፤ የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤
25 ፤ የሚካ ልጅ ሻሚር፤ የሚካ ወንድም ይሺያ፤
26 ፤ ከይሺያ ልጆች ዘካርያስ፤ የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ፤ ከያዝያ ልጅ በኖ፤
27 ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም፥ ዘኩር፥ ዔብሪ፤
28 ፤ ከሞሖሊ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩት፤
29 ፤ ከቂስ፤ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል፤ የሙሲም ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ዔዳር፥ ኢያሪሙት።
30 ፤ እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ።
31 ፤ እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቢሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።