መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 4

የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚ፥ ሆር፥ ሦባል ናቸው።
2 ፤ የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው።
3 ፤ እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ።
4 ፤ የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የሑሻም አባት ኤጽር፤ እነዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጆች ናቸው።
5 ፤ ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።
6 ፤ ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው።
7 ፤ የሔላም ልጆች ዴሬት፥ ይጽሐር፥ ኤትናን ናቸው።
8 ፤ ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።
9 ፤ ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም። በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን። ያቤጽ ብላ ጠራችው።
10 ፤ ያቤጽም። እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
11 ፤ የሹሐም ወንድም ክሉብ የኤሽቶንን አባት ምሒርን ወለደ።
12 ፤ ኤሽቶንም ቤትራ ፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
13 ፤ የቄኔዝም ልጆች ጎቶንያልና ሠራያ ነበሩ። የጎቶንያልም ልጅ ሐታት ነበረ።
14 ፤ መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ። ሠራያም የጌሃራሽምን አባት ኢዮአብን ወለደ፤ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ።
15 ፤ የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ።
16 ፤ የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ።
17 ፤ የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ።
18 ፤ አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
19 ፤ የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ።
20 ፤ የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ።
21 ፤ የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥
22 ፤ ዮቂም፥ የኮዜባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ ሞዓብን የገዛ ሣራፍ፥ ያሹቢሌሔም ነበሩ።
23 ፤ ይህ ዝና ከቀድሞ ጀምሮ ነበረ። እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ በንጉሡ ዘንድ ስለ ሥራው ይቀመጡ ነበር።
24 ፤ የስምዖንም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪን፥ ዛራ፥ ሳኡል፤
25 ፤ ልጁ ሰሎም፥ ልጁ መብሳም፥ ልጁ ማስማዕ።
26 ፤ የማስማዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙኤል፥ ልጁ ዘኩር፥ ልጁ ሰሜኢ።
27 ፤ ለሰሜኢም አሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፥ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም።
28 ፤ በቤርሳቤህም፥ በሞላዳ፥
29 ፤ በሐጸርሹዓል፥ በቢልሃ፥ በዔጼም፥
30 ፤ በቶላድ፥ በቤቱኤል፥ በሔርማ፥ በጺቅላግ፥
31 ፤ በቤትማርካቦት፥ በሐጸርሱሲም፥ በቤትቢሪ፥ በሸዓራይም ይቀመጡ ነበር። እስከ ዳዊትም መንግሥት ድረስ ከተሞቻቸው እነዚህ ነበሩ።
32 ፤ መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች፤
33 ፤ እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው።
34 ፤ ምሾባብ፥ የምሌክ፥ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያ፥
35 ፤ ኢዮኤል፥ የዮሺብያ ልጅ፥ የሠራያ ልጅ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ፥
36 ፤ ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ዩሲምኤል፥ በናያስ፥
37 ፤ የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ፤
38 ፤ እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር።
39 ፤ ለመንጎቻቸው መሰምርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌዶር መግቢያ እስከ ሸለቆው ምሥራቅ ድረስ ሄዱ።
40 ፤ የለመለመችም እጅግም ያማረች መሰምርያ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
41 ፤ እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰምርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።
42 ፤ የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።
43 ፤ ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ቅሬታ መቱ፥ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።