መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 2

የእስራኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥
2 ፤ ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር።
3 ፤ የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ከሴዋ ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም።
4 ፤ ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።
5 ፤ የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ሐሙል።
6 ፤ የዛራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ሄማን፥
7 ፤ ከልኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አምስት ነበሩ። የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።
8 ፤ የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ።
9 ፤ ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች፤ ይረሕምኤል፥ አራም፥ ካልብ ነበሩ።
10 ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤
11 ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤
12 ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤
13 ፤ እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥
14 ፤ አራተኛውንም ናትናኤልን፥
15 ፤ አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም አሳምን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ፤
16 ፤ እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ሦስቱ ነበሩ።
17 ፤ አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ዬቴር ነበረ።
18 ፤ የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ።
19 ፤ ዓዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ሆርን ወለደችለት።
20 ፤ ሆርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21 ፤ ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤
22 ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩት።
23 ፤ ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።
24 ፤ ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
25 ፤ የኤስሮምም የበኵር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኵሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ።
26 ፤ ለይረሕምኤልም ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርስዋም የኦናም እናት ነበረች።
27 ፤ የይረሕምኤል የበኵሩ የራም ልጆች መዓስ፥ ያሚን፥ ዔቄር ነበሩ።
28 ፤ የኦናምም ልጆች ሸማይና ያዳ ነበሩ። የሸማይ ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ።
29 ፤ የአቢሱርም ሚስት አቢካኢል ነበረች፤ አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት።
30 ፤ የናዳብም ልጆች ሴሊድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ያለ ልጆች ሞተ።
31 ፤ የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ።
32 ፤ የሸማይም ወንድም የያዳ ልጆች ዬቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዬቴርም ያለ ልጆች ሞተ።
33 ፤ የዮናታንም ልጆች ፌሌትና ዛዛ ነበሩ፤ እነዚህ የይረሕምኤል ልጆች ነበሩ።
34 ፤ ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው።
35 ፤ ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርስዋም ዓታይን ወለደችለት።
36 ፤ ዓታይም ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛባድን ወለደ፤
37 ፤ ዛባድም ኤፍላልን ወለደ፤ ኤፍላልም ዖቤድን ወለደ፤ ዖቤድም ኢዩን ወለደ፤
38 ፤ ኢዩም ዓዛርያስን ወለደ፤
39 ፤ ዓዛርያስም ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስም ኤልዓሣን ወለደ፤
40 ፤ ኤልዓሣም ሲስማይን ወለደ፤
41 ፤ ሲስማይም ሰሎምን ወለደ፤ ሰሎምም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
42 ፤ የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኵሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ።
43 ፤ የኬብሮንም ልጆች ቆሬ፥ ተፉዋ፥ ሬቄም፥ ሽማዕ ነበሩ።
44 ፤ ሽማዕም የዮርቅዓምን አባት ረሐምን ወለደ፤ ሬቄምም ሸማይን ወለደ።
45 ፤ የሸማይም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖንም የቤት ጹር አባት ነበረ።
46 ፤ የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች።
47 ፤ ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። የያህዳይም ልጆች ሬጌም፥ ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ፥ ሸዓፍ ነበሩ።
48 ፤ የካሌብም ቁባት ማዕካ ሸቤርንና ቲርሐናን ወለደች።
49 ፤ ደግሞም የመድማናን አባት ሸዓፍንና የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ ዓክሳ ነበረች።
50 ፤ የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሦባል፥
51 ፤ የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዴር አባት ሐሬፍ።
52 ፤ ለቂርያትይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኵሌታ።
53 ፤ የቂርያትይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ።
54 ፤ የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮትቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኵሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ።
55 ፤ በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።