መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 8

ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥
2 ፤ ሦስተኛውንም አሐራን፥ አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ።
3 ፤ ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥
4 ፤ ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም።
5
6 ፤ እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤
7 ፤ ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሒሑድን ወለደ።
8 ፤ ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ።
9 ፤ ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥
10 ፤ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
11 ፤ ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።
12 ፤ የኤልፍዓልም ልጆች፤ ዔቤር፥ ሚሻም፥ ኦኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ፤
13 ፤ በሪዓ፥ ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤
14 ፤ አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥
15
16 ፤ ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች፤
17 ፤ ዝባድያ፥ ሜሱላም፥
18 ፤ ሕዝቂ፥ ሔቤር፥ ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ የኤልፍዓል ልጆች፤
19 ፤ ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥
20
21 ፤ ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች፤
22 ፤ ይሽጳን፥
23 ፤ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ ዓብዶን፥ ዝክሪ፥
24
25 ፤ ሐናን፥ ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ ይፍዴያ፥ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤
26 ፤ ሸምሽራይ፥
27 ፤ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች።
28 ፤ እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
29 ፤ የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥
30 ፤ የበኵር ልጁ ዓብዶን፥
31 ፤ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር በገባዖን ተቀመጡ።
32 ፤ ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።
33 ፤ ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ።
34 ፤ የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
35 ፤ የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።
36 ፤ አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
37 ፤ ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤
38 ፤ ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
39 ፤ የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት።
40 ፤ የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኃያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።