መጽሐፈ አስቴር።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10


ምዕራፍ 10

ንጉሡም አርጤክስስ በምድርና በባሕር ደሴቶች ላይ ግብር ጣለ።
2 ፤ የኃይሉና የብርታቱም ሥራ ሁሉ ንጉሡም እስከ ምን ድረስ እንዳከበረው የመርዶክዮስ ክብር ታላቅነት፥ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
3 ፤ አይሁዳዊውም መርዶክዮስ ለንጉሡ ለአርጤክስስ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤ በአይሁድም ዘንድ የከበረ፥ በብዙ ወንድሞችም ዘንድ የተወደደ፥ ለሕዝቡም መልካምን የፈለገ፥ ለዘሩም ሁሉ በደኅና የተናገረ ነበረ።