መጽሐፈ ነህምያ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13


ምዕራፍ 10

ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ ሐቴርሰታ ነህምያ፥
2 ፤ ሴዴቅያስ፥ ሠራያ፥
3 ፤ ዓዛርያስ፥ ኤርምያስ፥ ፋስኮር፥ አማርያ፥ መልክያ፥
4
5 ፤ ሐጡስ፥ ሰበንያ፥ መሉክ፥ ካሪም፥
6 ሜሪሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥ ጌንቶን፥ ባሮክ፥
7
8 ፤ ሜሱላም፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቤልጋል፥ ሸማያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ።
9 ፤ ሌዋውያኑም፤ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኤንሐዳድ ልጆች ቢንዊ፥ ቀድምኤል፤
10 ፤ ወንድሞቻቸውም ሰባንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣስ፥
11 ፤ ፌልያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረአብ፥ ሐሸብያ፥
12
13 ፤ ዘኩር፥ ሰራብያ፥ ሰበንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒ፥ ብኒኑ።
14 ፤ የሕዝቡ አለቆች፤ ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥
15 ፤ ኤላም፥ ዛቱዕ፥ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥
16
17 ፤ አዶንያስ፥ በጉዋይ፥ ዓዲን፥ አጤር፥ ሕዝቅያስ፥
18 ፤ ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፥
19
20 ፤ ሐሪፍ፥ ዓናቶት፥ ኖባይ፥ መግጲዓስ፥ ሜሱላም
21
22 ፤ ኤዚር፥ ሜሴዜቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፥ ፈላጥያ፥
23 ፤ ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ አሱብ፥
24
25 ፤ አሎኤስ፥ ፈልሃ፥ ሶቤቅ፥ ሬሁም፥ ሐሰብና፥
26
27 ፤ መዕሤያ፥ አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ መሉክ፥ ካሪም፥ በዓና።
28 ፤ የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ታላላቆቻቸው ተጠጉ፤
29 ፤ በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ።
30 ፤ ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፤
31 ፤ የምድርን አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ የሰባተኛውንም ዓመት ፍሬና ዕዳን ማስከፈል እንተዋለን ብለው ማሉ።
32
33 ፤ ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቍርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን።
34 ፤ እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤
35 ፤ በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
36 ፤ በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
37 ፤ የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቍርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
38 ፤ ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
39 ፤ የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቍርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።