በመተኛት ድምጽ
- ፤ ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። ፤ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል። [መጽሐፈ ኢዮብ። 11:18,19]
- እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ። [መዝሙረ ዳዊት 3:5]
- በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና። [መዝሙረ ዳዊት 4:8]
- ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ [መዝሙረ ዳዊት 91:5]
- በተኛህ ጊዜ አትፈራም፤ ትተኛለህ፥ እንቅልፍህም የጣፈጠ ይሆንልሃል። [መጽሐፈ ምሳሌ 3:24]