ወደ እግዚአብሔር መጮህ
- ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። [መዝሙረ ዳዊት 9:10]
- ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው። [መዝሙረ ዳዊት 34:17]
- ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ። [መዝሙረ ዳዊት 86:7]
- ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። [መዝሙረ ዳዊት 91:15]
- እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም። [መዝሙረ ዳዊት 145:18, 19]