ቃል
- 
 አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። 
 መዝሙረ ዳዊት 119:11
- 
የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል። 
 መዝሙረ ዳዊት 119:130
- 
እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። 
 የማቴዎስ ወንጌል 4:4
- 
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። 
 የማቴዎስ ወንጌል 24:35
- 
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ...ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። 
 የዮሐንስ ወንጌል 1:1,14
- 
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
 የዮሐንስ ወንጌል 6:63
- 
እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤ 
 የዮሐንስ ወንጌል 15:3
- 
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 
 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:15
- 
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ 
 ወደ ዕብራውያን 4:12
- 
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። 
 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:3